ድፍረት ፊልም በፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ ተላለፈበት : የፊልሙ ምረቃ ዝግጅትም ተቋረጠ

(አዲስኒውስ) – ከስድስት ዓመት በላይ ለመሰናዶ የወሰደው፣ በርካታ የፊልም ባለሙያዎች የተሳተፉበት፣  ከሃገር ውጪ ሲታይ ሰንብቶ ዝናን የተጎናጸፈው እና በከሁለት ቀናት በፊት በብሔራዊ ትያትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም ባለታሪኳ የእኔን ፍቃድ አላገኝም በማለት ባቀረበቺው ክስ መሰረት ፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ አስተላለፈበት፡፡
 በብሔራዊ ቴያትር በልዩ ተጋባዦች፣ በሚኒስቴሮች፣ በዲፕሎማቶች፣ በጥበብ ሰዎች እና ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች ሊመረቅ የነበረው የድፍረት ፊልም ከፍርድ ቤት በመጣ ትዕዛዝ ምክንያት የምረቃ ፕሮግራሙ ተቋርጦ ሳይመረቅ ቀርቷል፡፡ የአዲስኒውስ ዘጋቢ የክስተቱ መነሻ የሆነውን ምክንያት ለማጣራት ሞክሮ እንዳጠናቀረው የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቴያትር ዳሬክተር አቶ ተሰፋዬ ሺመልስ እንደነገሩኝ እንግዶች፣ ሚንስቴሮች፣ ዲፕሎማቶች ፣ የጥበብ ሰዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዦች ቦታ ቦታቸውን ይዘው የሰነ ሥርዓቱን መጀመር ሲጠባበቁ በደረሰኝ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት ፊልሙን ማሳየት እንደማንችል ተናግሪያለሁ ብለዋል፡፡ ዝርዝር ምክንየቱ ግን እኔን ስለማይመለከተኝ ምንም ማለት አልችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከፍርድ ቤት በተገኝ መረጃ መሠረት በፊልሙ ላይ የዕግድ ትዕዛዝ ሊወጣበት የቻለው የፊልሙ ታሪክ ከባለታሪኳ አበራሽ በቀለ ፍቃድን ባለማግኘቱ ባለታሪኳ የህልውና እና የህግ ከለላ ጥያቄ በማንሳት ለፌዴራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት ልድታ ምድብ ችሎት ባቀረበቺው ክስ መሠረት መሆኑ ታዉቋል፡፡ የፊልሙን ደረሲና ዳሬክተር አቶ ዘረሰናይ መሃሪ ሰለጉዳዩ እንዲያስረዱኝ ብጠይቃቸውም አሁን ምንም ነገር መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸውልኛል፡፡

Difret-film-Ethiopia-Premier
የድፍረት ፊልም ባለታሪክ የሆነችውን የአበራሽ በቀለ የፍርድ ቤት መዝገብ አግኝቼ እንደተረዳሁት ጉዳዩ ከአስራ ስምንት ዓመት በፊት ማለትም በ1988 ዓ.ም የተፈጸመ ሲሆን “በአሰላ ዞን ሙኒሳ በምትባል ወረዳ ነዋሪ የነበረቺው አበራሽ በቀለ ጥቅምት 3 ቀን 1988 ዓ.ም ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ላይ በነበረቺበት ውቅት አቶ ገመቹ ከበደ የተባለ ግለሰብ ከአስራ አንድ ባልደረቦቹ ጋር በመሆነ ጠልፈው ይወስዷታል፡፡ ወደ ቤቱ ከወሰዳት እና አሰገድዷት ከደፈራት በኃላ ልጆች እንዲጠብቋት በመንገር ቡና ለመጠጣት ወደ ጎረቤት በሄደበት ወቅት አበራሽ በቤቱ ውስጥ ያገኝቺውን ሽጉጥ በመያዝ ከቤት ወጥታ እሩጫ ትጀምራለች፤ ይህን የተመለከቱት ሲጠብቋት የነበሩት ልጆችም ቡና ሲጠጣ ለነበረው አቶ ገመቹ ይነገሩታል፡ እሱም አበራሽን ለመያዝ ይከታተላት ጀመር፡፡ ሽጉጡን ወደ ሰማይ በመቶከስ እንዳይከተላት ለመከላከል ብትሞክርም እየቀረባት በመምጣቱ ሽጉጡን ቀጥታ ወደ አቶ ገመቹ በማዞር በተኮሰችው ጥይት አቶ ገመቹ  በመመታቱ ይሞታል፡፡”ከመዝገቡ የተረዳሁት ታሪክ ይህ ሲሆን “የወረዳው ዐቃቤ ህግም አበራሽን በነፍስ ግድያ ክስ እንደ መሰረተባት እና አበራሽ በወቅቱ በራሷ ፍርድ ቤት ቆማ ለመከራክር አቅሙ ስላልነበራት የኢትዮጲያ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ጠበቃ መድቦ ተከራክሮላታል፡፡ በዚህም መሠረት የአሰላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 7 ቀን 1990 ዓ.ም. በዋለዉ ችሎት አበራሽ እርምጃውን የወሰደችዉ ራሷን ለመከላከል መሆኑን ፍርድ ቤቱ አምኖበት በነፃ ተለቃለች፡፡” ይላል የድፍረት ፊልም ባለታሪክ የአበራሽ በቀለ የፍርድ ቤት ውሳኔ፡፡ ድፍረት ፊልምም ይህን እውነተኛ ታሪክ በመውሰድ የተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዘረሰናይ መሃሪ ተፅፎ የተዘጋጀውና በእውቋ የሆሊዉድ የፊልም ተዋናይ አንጄሊና ጆሊ ፕሮዲዩስ  የተደረገው ድፍረት ፊልም በ64ኛው የበርሊን ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል እና የሰንዳንስ የተመልካቾች ምርጫ ሽልማት አሸናፊ ሲሆን በ ሳንፍራንሲስኮ የአለም አቀፍ ፊልም ፈስቲቫል ላይም የፊልሙ አዘጋጅ ዘረሰናይ መሃሪ በአዲስ አዘጋጅ ምድብ ለሽልማት እጩ ለመሆን የቻለበት ፊልም ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለእይታ በበቃባቸው ቦታዎች ሁሉ አድናቆት አግኝቷል፡፡
የፊልሙ ባለታሪክ አበራሽ በቀለ ፊልሙ ያለሷ ፈቃድ እንዲታይ እንደማትፈልግ ከሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ሰጥታ እንደነበር የፊልሙን መታገድ አዲስኒውስ.ኔት በዘገበበት ወቀት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ተሰጡ አስተያዬቶች ለመረዳት ችሏል:: ይህንን ቃለምልልስ የፊልሙ አዘጋጆች ይወቁ አይወቁ የታወቀ ነገር ባይኖርም የምረቃ ዝግጅቱ በተቋረጠበት ሰዓት ምንም አይነት ክስ በቅድሚያ እንዳልደረሳቸው የፊልሙ ዋና አዘጋጅ ዘረሰናይ መሃሪ መናገሩ ይታወሳል::

ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ቀናት በፊት በሀገር ውስጥ ሊታይ የነበረው ድፍረት በትላንቱ ምሽት ብቻ ከአንድ ሺ በላይ ተመልካቾች ይመርቁታል ተብሎ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ፊልሙ ጳጉሜ 1 እና 2 2006ዓ.ም. በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለመታየት ፕሮግራም ተይዞለት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

Difret Film Awards

Berlin International Film Festival 2014

Won
Panorama Audience Award
Fiction Film
Zeresenay Mehari
See Also:  Ethiopian Zeresenay to Direct the Romantic Drama ‘Sweetness in the Belly’

 

San Francisco International Film Festival 2014

Nominated
New Directors Prize
Zeresenay Mehari

 

Sundance Film Festival 2014

Won
Audience Award
World Cinema – Dramatic
Zeresenay Mehari
Nominated
Cinematography Award
World Cinema – Dramatic
Monika Lenczewska
Dramatic
Monika Lenczewska
Nominated
Grand Jury Prize
World Cinema – Dramatic
Zeresenay Mehari

 


AddisNews is not responsible for the contents or reliability of any other websites to which we get contents from and provide a link and do not necessarily endorse the views expressed by them.

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Send this to a friend