ድፍረት ፊልም እንደገና በፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ ተላለፈበት

(AddisNews) በዘረሰናይ መሃሪ ተፅፎ የተዘጋጀውና በእውቋ የሆሊዉድ ፊልም ተዋናይ አንጄሊና ጆሊ ፕሮዲዩስ  የተደረገው ድፍረት ፊልም በሲኒማ ቤቶች እንዳይታይ በድጋሚ ከፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ተላለፈበት፡፡
ፊልሙ ለሁለተኛ ጊዜ የዕግድ ትዕዛዝ የተላለፈበት የጠበቃ እታገኘ ለሜሳ ልጅ አቶ ብሩክ አስራት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ባቀረቡት ክስ መሰረት መሆኑም ታውቋል፡፡
 የአዲስኒውስ ዘጋቢ የክሱ ዝርዝሩን እንደሚተመለከተው የድፍረት ፊልም ባለታሪክ የሆነቺው ወ/ሮ አበራሽ በቀለ ከዛሬ አስራ ስድስት ዓመት በፊት በአርሲ ዞን በሙኒሲ ወረዳ የጠለፋና የአሰገድዶ መድፈር ተግባር የተፈጸመባት ሲሆን ይህ ድርጊት የፈጸመባትን ግለሰብ ቶክሳ በመግደሏ በተከሰሰችበት የሰው መግደል ውንጀል ክስ በፍርድ ቤት በመቆምና በመከራክር እንደታግዛት ዋና ቢሮውን አዲሰ አበባ ካደረገው የኢትዮጵያ ሴት የህግ ባለሙያዎች ማህበር ወ/ሮ እታገኘ ለሜሳ ተወክላ የሄድች ሲሆን የድፈረት ፊልም ባለታሪክ የሆነቺውን ወ/ሮ አበራሽ በቀለን ከተከሰሰቺበት ክስ በነጻ እንደትለቀቅ አድርጋለች፡፡ ነገር ግን ድፍረት ፊልም ሲሰራ ወ/ሮ እታገኘ ለሜሳ የሰራቸው ስራ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እንደሰራቸው ተደርጎ ቀርቧል ይላል የክሱ ዝርዝር፡፡
ይህን ክስ ያቀረበው የወ/ሮ እታገኘ ለሜሳ  ልጅ አቶ ብሩክ አሰራት ክሱን ለመመሠረት ምን እንዳነሳሳው ሲናገር “ድፍረት ፊልም መሰራቱን ካውቅን በኃላ የእናታችንን ልፋት ለሌላ ሰው ተሰጥቶ በማየታችን፣ በታሪኩ እናቴ ጠበቃ ሆና የተከራከረቺውን ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የእናቴን ታሪክ ያራሷ አድራጋ በማቅረቧ በእሷ እና ፊልሙን በሰሩት ግለሰቦች ላይ ክስ መስረተናል፡፡” ብሏል፡፡

Difret film
በዚህም መሠረት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ አቶ ዘረሰናይ መሃሪ፣ ሀይል አዲስ ሮች ድርጅትና ትሩዝ ኤድ የሚዲያ ድርጅትን ከአንደኛ እስከ አራተኛ በመዘርዘር ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ ሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ሀይል አዲስ ሮች ድርጅትና ትሩዝ ኤድ የሚዲያ ድርጅትን መቀመጫቸው አሜሪካን ሀገር መሆኑም ታውቋል፡፡
ክሱ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥቅምት 13 ቀን 2007ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ ያለውን ድፍረት ፊልምን የተያዘው ጉዳይ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረሰ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ በዚህም ለሁሉም ሲኒማ ቤቶች የዕግድ ትዕዛዙ እንዲደርሳቸው ታዟል፡፡

 
ድፍረት ፊልም ነሐሴ 28 ቀን 2006ዓ.ም በብሔራዊ ትያትር በመመረቅ ላይ እያለ እስራ አምስት የሚሆኑ ደቂቃዎች ብቻ ከታየ በኃላ ለቴያትር ቤቱ ከፍርድ ቤት በመጣ ትዕዛዝ መሠረት እንዲታገድ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በውቅቱም ለፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት የፊልሟ ባለታሪክ የሆነቺው ወ/ሮ አበራሽ በቀለ እና የወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ወንድም አቶ ፍቅሩ አሸናፊ ባቀረቡት ክስ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በክሱም ባለታሪኳ እኔን ሳያሳውቁኝ እና የእኔን ፍቃድ ሳያገኙ ፊልሙን ሰረተውታል ሰለዚህም የፊልሙ ጥቅም ይገባኛል ስትል የመብት ጥያቄ አንስታ የነበረ ሲሆን አቶ ፍቅሩ በበኩሉ የሀሳቡ አመንጪ ሆኜ እያለ ያለ እኔ ፍቃድና እውቅና ፊልሙ ተሰርቷል ሰለዚህም ከፊልሙ ጥቅም ተጋሪ መሆን አለብኝ ሲል የመብት ጥያቄ ያነሳ ሲሆን ጉዳዩ በፍርድ ቤት ከተያዘ በኃላ ጉዳዩን በሽምግልና ስለጨረሱ የክሱ መዝገብ እንዲዘጋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ድፍረት ፊልም በ64ኛው የበርሊን ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል እና የ 2014 ሰንዳንስ የፊልም ፌስቲቫል ድራማቲክ የተመልካቾች ምርጫ አሸናፊ ሆኖ ተሸላሚ የሆነ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አድናቆት ያገኘ ፊልም ነው፡፡

Difret Film Awards

Berlin International Film Festival 2014

Won
Panorama Audience Award
Fiction Film
Zeresenay Mehari

 

San Francisco International Film Festival 2014

Nominated
New Directors Prize
Zeresenay Mehari

 

Sundance Film Festival 2014

Won
Audience Award
World Cinema – Dramatic
Zeresenay Mehari
Nominated
Cinematography Award
World Cinema – Dramatic
Monika Lenczewska
Dramatic
Monika Lenczewska
Nominated
Grand Jury Prize
World Cinema – Dramatic
Zeresenay Mehari

 


AddisNews is not responsible for the contents or reliability of any other websites to which we get contents from and provide a link and do not necessarily endorse the views expressed by them.

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share to Friends

Send this to a friend