ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

Addis market car for sale in ethiopia addis ababa

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

Engineer Simegnew Bekele killed in his car

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ፣ 19፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል በኢንጂነር ስመኘው በቀለ አሟሟት ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

በሰጡት መግለጫም ኢንጂነር ስመኘው ከጆሯቸው በስተጀርባ በኩል በጥይት ተመተው ህይዎታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

አሁን ላይም ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት የተለያዩ አሻራዎችንና ማስረጃዎችን በመውሰድ እያጣራ ይገኛል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ኢንጂነር ስመኘው ህይወታቸው ከማለፉ ቀደም ብሎ ማለዳ ላይ ቢሮ እንደነበሩም ጠቅሰዋል።

የአስክሬን ምርመራ በጳውሎስ ሆስፒታል እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ የፎሬንሲክና የአሻራ ምርመራ በሳይንሳዊ መንገድ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

የፖሊስ አባላትም ጉዳዩን ለማጠራት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ እንደሆነ ነው ኮሚሽነሩ የጠቆሙት።

ህብረተሰቡም ፖሊስ ዝርዝር ጉዳዩን አጣርቶ ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ ተረጋግቶ እንዲጠብቅም አሳስበዋል።

ከዚህ ባለፈ በአካባቢው የነበረው የደህንነት ካሜራ በትናትናው ዕለት ተነስቷል የሚለው የተሳሳተ መሆኑን በመግለፅ ካሜራው ከመንገድ ግንባታ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት መነሳቱን ተናግረዋል።

RELATED: Ethiopian Nile dam manager Simegnew Bekele found dead in his car


“Engineer Simegnew Bekele was found dead in his car this morning in Meskel Square. His body has been taken to hospital for an autopsy,” Fana Broadcasting Corporation said, referring to an area in the center of the capital.

ምንጭ፥ ፋና ፌስቡክ ገጽ


AddisNews is not responsible for the contents or reliability of any other websites to which we get contents from and provide a link and do not necessarily endorse the views expressed by them.

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share to Friends

Send this to a friend