ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ፓርላማ ተጋብዘዋል ወይስ አልተጋበዙም ? አና ጎሜዝ ይመልሳሉ

Ana-Gomes-birhanu-nega-voa-amharic
በትናንትናው ዕለት በቤልጅየም ብራስልስ ከተማ በአውሮፓ ፓርላማ ተገኝተው በሃገሪቱ ላይ ስለተከሰተው የረሃብ ሁኔታ ገለጻ ያደረጉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፓርላማው ነው ወይስ በግል በወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው የተጋበዙት የሚለው ክርክር ተባብሶ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ቢሮ ፕሮፌሰሩ በአውሮፓ ፓርላማ አልተጋበዙም የሚል አጭር መግለጫ አውጥቷል::
ይህንን መግለጫም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ በማውጣት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኦፊሴላዊ ጥሪ እንዳልተደረገላቸውና በበልጂየም ብራሰልስ ንግግር ሊያደርጉ ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አስተባብሏል::

EU Ethiopia on Birhanu nega invitation

ይህ የወጣው መግለጫ ቃል በጥቅሉ በአማርኛ ሲተረጎም :
” የአውሮፓ ህብረት አቶ ብርሃኑ ነጋ ወደ ብራሰልስ በአውሮፓ ፓርላማ አባል በሆኑ ግለሰብ የግል ግብዣ የመጡ እንጂ በፓርላማው በይፋ እንዳልተጋበዙ እና የሚወክሉትን ድርጅት እንቅስቃሴ እውቅና እንደማይሰጠው ለማሳወቅ ይወዳል:: የአውሮፓ ህብረት በማንኛውም ሰላማዊ ያልሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ (ሃሳብ) ይቃወማል::”

ይህንን መግለጫ በመጥቀስ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ሪፖርተር ጽዮን ግርማ ሁኔታውን ለማጣራት ከወ/ሮ አና ጎሜዝ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ የፓርላማ አባሏ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በስብሰባው ላይ የተገኙት በግል ግብዣ ሳይሆን በአውሮፓ ፓርላማ አባላት ግብዣ እንደሆነ ማረጋገጣቸውን በቪኦኤ ድረ ገጽ ላይ ተገልጿል::

አና ጎሜዝ አክለውም “ድርቅና ረሃብ በኢትዮጵያ” (Famine and Drought in Ethiopia) በሚል አሁን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ረሃብ በቤልጅየም ብራስልስ በአውሮፓ ፓርላማ ፊት የተካሄደው ውይይት እና ክርክር ጥሩ እንደነበር ገልጸው ፕሮፈሰሩም በምን ሁኔታ እንደተገኙ አብራርተዋል::

በዚህ ስብሰባ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር እንዲገኙ ተጋብዘው የነበረ ሲሆን ኤምባሲው በአምባሳደሩ ምትክ ተወካይ እንደላኩ እና የውይይቱ ተካፋይ እንደነበር ተገልጿል::
ኢትዮጵያን ወክሎ በዚህ ስብሰባ ላይ የተካፈለው ተወካይ የውጭ ሃገር ተወላጅ መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ግርምትን ፈጥሯል::

ወ/ሮ አና ጎሜዝ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ስለጉዳዮ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ::
Watch European Parliament member Ana Gomes interview on the invitation of Professor Birhanu Nega

Professor Birhanu Nega Interview about his European Parliament discussion with VOA Amharic Service

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share to Friends

Send this to a friend