በጎንደር ከተማ ወህኒ ቤት በተነሳ ቃጠሎ በተያያዘ እስረኞች ተገደሉ ( ቪዲዮ)

በጎንደር ከተማ ወህኒ ቤት በተነሳ ቃጠሎ በተያያዘ እስረኞች ተገደሉ
በጎንደር ከተማ የሚገኘው እና ባህታ ተብሎ በሚጠራው ወህኒ ቤት ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በተያያዘ ከ 20 የማያንሱ እስረኞች እስካሁን ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ወይም በተነሳው እሳት እንደሆነ በውል ባልታወቀ ምክንያት ተገድለዋል:: በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችም ከእስር ቤቱ እንዳመለጡ እየተነገረ ነው::

የከተማው ነዋሪ እሳቱን ለማጥፋት ወደ እስር ቤቱ ገብቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በከተማው ውጥረት እንደነገሰ በቦታው የሚገኝ ነዋሪ ለአዲስኒውስ ገልጿል::

በተያያዘ ዜና በሃረማያ ዩንቨርሲቲ አዲሱን የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ ተማሪዎች ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት የፖሊስ ሃይሉ ተማሪዎችን መደብደብ እና ማቁሰላቸው እየተዘገበ ነው::
በዚህ የአዲስ አበባ አከላለል ጉዳይ ላይ በኦሮሚያ ውስጥ በባሌ በነቀምት እና የተለያዪ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል::

nekemte town protest police
በነቀምት ከተማ የፌደራል ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ተማሪዎችን አግተዋል:; ፎቶ ምንጭ: ትዊተር

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Send this to a friend