በኦሮሚያ የተማሪዎች ተቃውሞ ፖሊስ እስካሁን አንድ ተማሪ ብቻ መግደሉን መንግስት አስታወቀ

የሃረማያ ዩንቨርሲቲን ጨምሮ በወላቡ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም፥ በምእራብ ሸዋ እና በምእራብ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲሱን በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞችን በአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን መካተትን በመቃወም ለሰልፍ የወጡትን ተማሪዎች ለመበተን በተወሰደው እርምጃ እስካሁን አንድ ተማሪ ብቻ መገደሉን መንግስታዊው ፋና ብሮድካስቲንግ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን በመጥቀስ ዘገበ::

ተማሪዎቹ የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጃ የጋራ ማስተር ፕላን የተባለው ፕላን ነዋሪዎችን ያለ አግባብ ከመሬታቸ በማፈናቀል ከተማዋን ለማስፋፋት ለማድረግ የታለመ ነው በሚልና በክልሉ የመልካም አስተዳደር ችግር በመኖሩ የተፈጠረ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ከጀርመን ሬዲዮ የአማርኛው ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይከሳሉ::
ካለፍነው ሰኞ ጀምሮ በክልሉ ውስጥ የተቃውሞ ድምጻቸውን ባሰሙ ተማሪዎች እና ፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት የፖሊስ ሃይሉ ተማሪዎችን ላይ ጥይት ሲተኩሱ : መደብደብ እና ማቁሰላቸውን የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ በብዛት ተሰራጭተዋል::

ፋና ሁከት ባለው የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገደለው ወጣት በምእራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጨልያ በተባለ አከባቢ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ጨምሮ ገልጿል::

የአካባቢው ነዋሪዎች ከጀርመን ሬዲዮ የአማርኛው ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ

በዚህ የአዲስ አበባ አከላለል ጉዳይ ላይ በኦሮሚያ ውስጥ በባሌ በነቀምት እና የተለያዪ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል::

oromia protest  nekemt 2

oromia protest  nekemt 1

Related posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Send this to a friend